ዝክረ አበው
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ‘’ሊቀ ጳጳስ ዘ ደ ቡ ብ ኢትዮጵያ’’ በ መ ባ ል ይ ታ ወ ቁ የነበረ ሲሆን መ ን በ ረ ጵጵስናቸውም በነበረችው የጠቅላይ ግዛቱ ዋና ይርጋ ዓለም ከተማ ነበር። በቀድሞ ስማቸው ጌታሁን ወልደሐዋርያት ይባሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ ቀዳማዊ የተወለዱት ጥቅምት 7 ቀን 1889 ዓ.ም ከአባታቸው አቶ ወልደሐዋርያት ዓለምነህ እና ከእናታቸው እመት ወለተሐና አብዬ ሆይ ነበር። የትውልድ ሥፍራቸውም በቀድሞ መንዝና ቡልጋ አውራጃ፤ በወለሌ ልዩ ስሙ መርፈታ በተሰኘ ቀበሌ ተወለዱ።
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ትምህርት ቤት ተላኩ፤ በዚያው በአካቢያቸው እስከ ዜማ ድረስ የሚሰጠውን የመጀመሪያ ደርጃ ትምህርት በሚገባ አጠናቀው ጨርሰው። በመቀጠል ለከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ጎጃም ብቸና አቅንተው ከእውቁ የቅኔ ሊቅ መምህር ውብሸት (የኔታ ውብሸት) በብቸና ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። ከዚያም ወደ በጌምድር፤ ጎንደር በመሻገር በጋይንት ማኅበረ በኩር በተባለ ሥፍራ ከፍ ያለውን የቅኔ ትምህርት ከአለቃ ምሥራቅና አለቃ ዓምደ ብርሃን ዘንድ ተማሩ። ቀድሞ በቡልጋ ተምረው የነበረውን የዜማ ትምህርትም አስፋፉት። ቀጥለውም አምስቱን የቅዱስ ያሬድን መጻሕፍት ድጓ፤ ጾመ ድጓ፤ ምእራፍ፤ ዝማሬና መዋስዕትን ጨርሰው ቅዳሴ እና አቋቋም በመማር በእነዚህ ትምህርቶች በመምህርነት ተመርቀዋል። በኋላም በጐንደር ጠቅላይ ግዛት ልዩ ስሙ እንዳቤት በተባለ ስፍራ በዘቦዬ ሚካኤል ደብር ለሰባት ዓመት አስተምረዋል። በዚህም በርካታ ተተኪ አገልጋዮችን አፍርተዋል።
ይቀጥላል . . .